የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ካቢኔ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

By Melaku Gedif

November 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ካቢኔ 4ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው በኮሪደር ልማት አካባቢ ያሉ የግል ባለይዞታዎች የቅድሚያ የማልማት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት አግባብ፣ የተጀመሩ ግንባታዎች የቦታ ማስፋፊያ ጥያቄዎች፣ ለኃይማኖት ተቋማት እና የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የቦታ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸዉ አኳያ በመመርመር እንዲፈቀድላቸው እና ወደ ልማት እንዲገቡ ውሳኔ አሳልፏል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለማስተዳደርና ለማልማት የወጣው ረቂቅ ደንብን መርምሮ ለማህበረሰቡ ከሚኖራቸው የጎላ አገልግሎት አኳያ በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተግባሪነት እንዲፈፀም መወሰኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።