አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ የቀብር ሥነ-ስርዓት ተፈጽሟል፡፡
በስነ-ሥርዓት ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ ሞሃመድ ሕልፈት ትናንት የተሰማ ሲሆን፥ በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያና ሶማሊላንድን ግንኙነት በማጠናከር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት አሕመድ ሞሃመድ ሞሃመድ፥ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደነበሩም ነው የተነገረው፡፡