አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ የተፈጠረው የአየር ብክለት ከተማዋን ጭጋግ በማልበስ ለእንቅስቃሴ አዳጋች ሁኔታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዴልሂ ከተማ የዓለም ጤና ድርጅት ለመተንፈስ አዳጋች ነው በሚል ካስቀመጠው የአየር ብክልት ደረጃ በ15 እጥፍ የሚልቅ መሆኑ ተነግሯል፡፡
አደገኛ የተባለው ይህ ብክለት የአየር በረራ አገልግሎቶች እንዲሰረዙ ማስገደዱ ተገልጿል።
በተጨማሪም የግንባታ ስራዎች እንዲቋረጡ የተደረገ ሲሆን ትምህርት ቤቶች በጊዜያዊነት እንዲዘጉም ተደርጓል።
በተጨማሪም በአገልግሎት ዘርፉ የተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ከቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
የተከሰተው የአየር ብክለት በመጪዎቹ ቀናት የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ባለፈው ሳምንት የህንድ መንግስት ማህበረሰቡ የድንጋይ ከሰል እንዲሁም የማገዶ እንጨት እና ጀነሬተሮችን አንዳይጠቀም እገዳ አስተላልፏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።