Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሺንትስ ኩባንያ የሰራተኞቹን ቁጥር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያው ሺንትስ ኩባንያ በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚያከናውነው የማስፋፊያ ስራ የሰራተኞቹን ቁጥር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ከሺንትስ ኩባኒያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ኩባንያው ለሚያከናውናቸው አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እና የማስፋፊያ ስራዎች ኮርፖሬሽኑ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻ ሼዶችን በመውሰድና ከ2 ቢሊየን ብር በላይ መዋዕለ ነዋይ ስራ ላይ እያዋለ የሚገኘው ሺንትስ የጨርቃጨርቅና ጋርመንት ኩባንያ ከ8 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረም ተገልጿል፡፡

በቀጣይም በሚያከናውነው ተጨማሪ የማስፋፊያ ተግባራት የሰራተኞቹን ቁጥር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኩባንያው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያስገነባቸውን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ማዕከላትል እንደሚያስመርቅም ተጠቁሟል፡፡

ሺንትስ ጋርመንት እና ቴክስታይል ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው አልባሳትን በማምረት በአሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በእስያ ሀገራት ምርቶቹን የሚያቀርብ ኩባንያ ነው፡፡

Exit mobile version