አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚመሩ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች በዛሬው ዕለት መጎብኘታቸውን አንስተዋል፡፡
ዕሴት በተጨመረበት ቡና ኤክስፖርት እና ብረታ ብረት ምርት ላይ የተካነው ኤኤምጂ ሆልዲንግስ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግሉ ዘርፍ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በመስታወትና በአሉሚኒየም ሥራዎች የሚታወቀው አንድነት መስታወት ቴክኖሎጂ የግሉ ዘርፍ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት እያበረከተ ላለው አስተዋጽዖ ማሳያ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡