አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ለመገምገም አሶሳ ከተማ ገብተዋል።
አመራሮቹ አሶሳ ሕዳሴ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታም የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ ሥራ አቅጣጫና መመሪያ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና የሁሉም ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዎች በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።