Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባሕርዳር የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር የለም – የመከላከያ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕርዳር የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር አለመኖሩን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷የኢፌዴሪ አየር ሃይል ካሉት “ቤዞች” አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድብ መሆኑን አንስቷል፡፡

በትላንትናው ዕለት በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ የነበር መሆኑን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

መደበኛ በረራ ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን÷ የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቅቋል ብሏል።

“የጠላት ሁለንተናዊ አቅምና የፕሮፖጋንዳ መስክ መክሰርና መከስከስ ካልሆነ በስተቀር የተከሰከሰ ሄሊኮፕተር የለም” ሲልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

Exit mobile version