የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስና አቶ ደስታ ሌዳሞ የሃዋሳ ከተማን የኮሪደር ልማት ሥራ ጎበኙ

By amele Demisew

November 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሃዋሳ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ምልከታ አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም በሃዋሳ ከተማ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሥራ ባህልን የቀየረና የከተማዋን ገፅታ ውብ ማድረግ እንደሚያስችል አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በተከናወነው ሥራ እንደተመለከቱ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።