አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በቀድሞ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ ሞሃመድ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ የኢትዮጵያና ሶማሊላንድን ግንኙነት በማጠናከር በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ
የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ቤተሰቦች እና ለመላው ሶማሊላንድ ሕዝብም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡