የሀገር ውስጥ ዜና

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀ

By Feven Bishaw

November 17, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን መወጣቱ ተገልጿል፡፡

ታላቁ ሩጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፣ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላትም የፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡