የሀገር ውስጥ ዜና

ማዕከሉ የዲኤንኤ ምርመራና የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል – ም/ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Mikias Ayele

November 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፎረንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከል ለጎረቤት ሀገራትም የዲኤንኤ ምርመራና የአቅም ግንባታ ስልጠና አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ የተመረቀው የፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከል እንደ ሀገር የተጀመረው የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ሪፎርም በርካታ ስኬቶች ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።

ተቋሙ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራትም የዲኤንኤ ምርመራና በዘርፉ የአቅም ግንባታ ስልጠና አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ተግባሩን ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ለመራችሁ፣ ለከወናችሁ እና ለደገፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።