Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከዲኤንኤ ጋር በተያያዘ የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዲኤንኤ ጋር በተያያዘ የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ የፎሬንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን መርቀናል ብለዋል።

ከአንድ አመት ተኩል በፊት እንደ ሀገር የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ እንደነበር አስታውሰው፤ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥማት በራሷ መስራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል በማለት ገልጸዋል።

ይህ በጸጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ባለፉት አመታት የሰራናቸው የሪፎርም ስራዎች ውጤት ነው ሲሉ አመልክተዋል።

Exit mobile version