አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲዳማ ሀገረ ስብከት ይርጋዓለም ደብረ ታቦር ኢየሱስ ወደብረ መንክራት ቅድስት አርሴማ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባዔ የተገነባው ጽሩይ የሳሙናና ዲተርጄንት ፋብሪካ ተመረቀ፡፡
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ፋብሪካውን መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የሐይማኖት ተቋማት በልማት ሥራዎች መሳተፋቸው በልማት ራስን የመቻልና ከልመና የመውጣትን ተሞክሮ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።
ፋብሪካው ቤተ ክርስቲያኗ ድህነትን ለመቀነስ በኢንዱስትሪ ልማት የሚኖራት አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑን ያሳል ማለታቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ከማገዝ ባሻገር ፋብሪካው ከ300 ለሚልቁ ወገኖች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የፕሮጀክቱ ኃላፊ ታደሰ ፋንታዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡