አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ጣሊያን ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከጣሊያን የልማት ድርጅት ዳይሬክተር ማክሮ ማስኮኒ ጋር በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ካለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ጎን ለጎን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ጣሊያን ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡
በጣሊያን የልማት ድርጅት በኩልም 25 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ዕቅድ እንደተያዘ አስረድተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በበኩላቸው የጣሊያን መንግሥት ለኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመሥግነው÷ ድጋፉ በአረንጓዴ ዐሻራና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ለሚከናወኑ ተግባራት ዕገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡