Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የውድድሩ መነሻ እና መድረሻ መቀስል ዐደባባይ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ÷ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከታች የተዘረዘሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል፡፡

-ከኦሎምፒያ ዐደባባይ ወደ መስቀል ዐደባባይ (ኦሎምፒያ ዐደባባይ )

–  ከጥላሁን ዐደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን ዐደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ

–   ከአፍሪካ ኅብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ ዐደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )

-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )

–  ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )

– ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )

-ከሴቶች ዐደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች ዐደባባይ )

–  ከሴቶች ዐደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች ዐደባባይ )

–  ከ22 ዐደባባይ ወይም ዘሪሁን ሕንጻ ወደ ዑራኤል ዐደባባይ (ዘሪሁን ሕንጻ መስቀለኛ )

–  ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል ዐደባባይ (ፒኮክ መብራት)

–  ከጋዜቦ ዐደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ ዐደባባይ)

–  ከቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤተ ክርሰቲያን ነርክ ተራ )

–  ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት  (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )

–  ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ ዐደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )

–  ከአፍሪካ ኅብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ ዐደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )

–   ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )

–  ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )

–  ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐደባባይ ወደ ሜክሲኮ ዐደባባይ (ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐደባባይ)

–  ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)

–  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)

–  ከሚቲዎሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሚቲዎሮሎጂ መታጠፊያ )

–  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)

–  ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)

–  ከቴዎድሮስ ዐደባባይ ወደ ሀገር አሥተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ ዐደባባይ)

ከንጋቱ 11 ሠዓት ከ30 ጀምሮ ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሠዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል፡፡

Exit mobile version