የሀገር ውስጥ ዜና

የወባ በሽታ የመከላከል ጥረትን የሚደግፍ መድሃኒት ከቻይና ይገባል ተባለ

By Melaku Gedif

November 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ኤይድ ፕሮጀክት በኩል ድጋፍ የተደረገ የወባ መድሃኒት በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከቻይና ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስል ዶ/ር ያንግ ዪሃን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የቻይና ትብብርና ወዳጅነት ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ዶ/ር ያንግ፤ የዶክትሬት ዲግሪ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

በትምህርት ዕድሉ ክልሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚኒስቴሩ ፍላጎት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ የቻይና ኤይድ ፕሮጀክት ያደረገው ድጋፍ የወባ መከላከል ጥረትን የሚደግፍ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም በቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ የኮሌራ ክትባት ለማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።