Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ የቱሪስት እና የኮንፈረንስ ቪዛዎች ላይ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ መደረጉ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ፡፡

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለማበረታታት በ2016 ዓ.ም በፀደቀው የኢሚግሬሽን ደንብ ቁጥር 550/2016 የአገልግሎት ዋጋ ተመን የዋጋ ቅናሽ መደረጉን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማስተዋል ገዳ አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የቱሪስት ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው 25 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ኢትዮጵያ በዓለም የቱሪዝም መዳረሻ ተመራጭ እንድትሆን እየተደረገ ባለው ጥረት የበኩሉን ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያን የዓለማችን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የኮንፈረንስ ቪዛ ክፍያ ከዚህ በፊት ከነበረው ተመን በ23 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያን ተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በሚከናወነው ሥራ ከላይ የተገለጹት ማሻሻያዎች የራሳቸውን ሚና እያበረከቱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version