አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች ሰላምን ለማጽናት የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ።
በሕዝባዊ ሰልፎ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ሰላምን ለማጽናት የበኩላችንን እንወጣለን፣ በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል፣ ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን አስተጋብተዋል።
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል።
በገላና ተስፋ