Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም ባንክ በሥራ ዕድል ፈጠራ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ በክኅሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት ወጣቶችንና ሴቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር መሪየም ሳሊም ጋር በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን የስራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም በክኅሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እና በተቋም ግንባታ የትኩረት መስኮች የተቀረጹ የሪፎርም አጀንዳዎችንና ግቦችን በዝርዝር ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ባንኩ እየተከተልን ባለነው የክኅሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት ወጣቶችንና ሴቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሯ አረጋግጠውልኛል ነው ያሉት፡፡

እንደ ሀገር እያከናወንን ባለነው ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ሂደት ባንኩ በሁሉም መስክ ተጨባጭ ድጋፎችን አድርጓል፤ አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሯ እንደ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችን በማላቅ የወጣቶችንና ሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላሳዩት ቁርጠኝነትም ሚኒስትሯ አመሥግነዋል፡፡

Exit mobile version