Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም ስማርት ፓርኪንግ ሲስተም ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን “ስማርት ፓርኪንግ ሲስተም” በሸገር ከተማ አሥተዳደር መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ አስጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የሸገር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

ሲስተሙ አሽከርካሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው በስልካቸው ባሉበት ሆነው የመኪና ማቆሚያ ቦታ መፈለግ፣ ፓርክ ማድረግ እና ክፍያ መፈጸም ያስችላቸዋል ተብሏል።

ክፍያውንም በቴሌብር ሱፐር አፕ መፈጸም እንደሚቻል ነው የተገለጸው።

ፍሬሕይወት ታምሩ ፥ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሸገር ከተማን ስማርት በማድረግ ሒደት የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የስማርት ፓርኪንግ ተግባራዊ መሆን ወሳኝ ነው ብለዋል።

ስማርት ፓርኪንግ ሲስተም በቴሌብር በስልክ መተግበሩ ጊዜን፣ ወጪን እና ድካምን እንደሚቀንስም አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው እና መሳፍንት እያዩ

Exit mobile version