አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይናዋ ጂያንሱ ግዛት ዋና ገዥ ሹ ኩሊን የተመራ የግዛቷ ከፍተኛ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
የጂያንሱ ግዛት ገዥ እና የግዛቷ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና መልሕቅ ኩባንያዎች አመራሮች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዛሬ በአዲስ አበባ በሚከፈተው የቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባዔ ላይም እንደሚሳተፍም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ጂያንሱ የቻይናዋ 2ኛዋ ግዙፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ግዛት ስትሆን 76 ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ በሚያወጡ የኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው እንደሚገኙ ተጠቁሟል።