ቢዝነስ

ላኪዎች ከነገ ጀምሮ ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ

By ዮሐንስ ደርበው

November 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሠራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ እንዳሉት÷ ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።

በወቅቱ አሠራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበርም አስታወሰዋል።

ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ማለት ብለዋል፡፡