Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ሀገራቸው ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ÷ የቱርክ ሪፐብሊክ ለረጅም ጊዜ ከእስራኤል ጋር ንግግር እንዳልነበረው አስታወሰው፤ አሁን ላይ ዲፕለማሲያዊ ግንኙነቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብለዋል፡፡

የጋዛ እና የሊባኖስን ጦርነት ስታወግዝ የቆየችው ቱርክ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የተኩስ አቁም እስከሚደረግ ድረስ ከእስራኤል ጋር ንግግር እንደማይኖራት ማመልከታቸውን ስፑትኒክ እና ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግበዋል፡፡

ቀደም ሲል በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ከእስራኤል ጋር ያላትን የወጪ እና ገቢ ንግድ ያቋረጠችው ቱርክ፤ ከእስራኤል ጋር በሚደረጉ ሌሎች የንግድ ልውውጦች ላይም ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

Exit mobile version