የሀገር ውስጥ ዜና

ከተሞችን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በሚሠራው ሥራ ትርጉም ያለው ርምጃ ተራምደናል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By ዮሐንስ ደርበው

November 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ በይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ተራምደናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2 ሺህ 879 ሔክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል ብለዋል።

በዚህም ከተሞቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ በይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል ነው ያሉት።

አሁን ላይም በሦስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሁለተኛ ደግሞ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ ነው ብለዋል፡፡

ሦስተኛው እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልኅቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት መሆኑን አብራርተዋል፡፡