Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኤሎን መስክ የመንግስት አፈፃፀም መምሪያ ሃላፊነት ሹመት በትራምፕ ተሰጣቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤክስ እና የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኤሎን መስክ የመንግስት አፈፃፀም መምሪያ ሃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ የአሜሪካ 47ኛው ፕሬዚዳንት በመሆን በተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

የዓለም ቁጥር አንድ ባለሀብቱ ኤሎን መስክ ከቀድሞው የሪፐብሊካን ተቀዳሚ እጩ ቪቪክ ራማስዋሚ ጋር በጋራ በመሆን መምሪያውን በሃላፊነት እንዲያገለግሉ መሾማቸው ተገልጿል።

መስክ በሃላፊነት ቆይታቸውም የሪፐብሊካን ፓርቲ የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች በተመለከተ ምክር እና መመሪያ በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግ እገዛ ያደርጋሉ መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኤሎን መስክ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከ1ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጭ በማድረግ የሪፐብሊካን ፓርቲን ሲደግፍ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ከኤሎን መስክ በተጨማሪ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የፎክስ ኒውስ አዘጋጅ እና የአሜሪካ ጦር የቀድሞ አባል የነበረውን ፔት ሄግሴዝ የአሜሪካ መከላከያ አድርገው ሲሾሙ፤ ጆን ራክሊፍን ደግሞ የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር ተደርገው ተሹመዋል።

Exit mobile version