የሀገር ውስጥ ዜና

ነገ ሶማሌላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች

By Feven Bishaw

November 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው እለት ሶማሌላንድ ለአራተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች ፡፡

ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ለመታዘብም ዓለምአቀፍ ታዛቢዎች ሶማሌላንድ ገብተዋል።

ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸው የተገለፀ ሲሆን÷13 ሺህ ምርጫ አስፈጻሚዎች እንዲሁም 2 ሺህ 648 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የሶማሌላንድ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

በስድስት ክልሎች በሚደረገው ምርጫ ህዝቡ ለፕሬዚዳንትና ለፓርቲ ድምጽ ይሰጣል።

የሶማሌላንድ ህዝቦች በየአምስት አመቱ ፕሬዚዳንታቸውን የሚመርጡ ሲሆን÷ በየአስር አመቱ ደግሞ ቀጣይ ለሁለት አምስት አመታት ለፕሬዚዳንትነት ምርጫ እጩ የሚያቀርቡ ሶስት ፓርቲዎችን ይመርጣሉ።

በነገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ኩልሚዬ፣ዋዳኒ እና ዩሲአይዲ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ።

በሶማሌላንድ ምስራቃዊ ክልሎች በተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ችግር በመኖሩ ምርጫ እንደማይካሄድባቸውም ምርጫ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በታሪኩ ለገሰ ከሃርጌሳ