የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሪደር ልማቱ ታሪካዊቷን የሐረር ከተማ አዲስ ገጽታ እንድትላበስ እያደረገ ነው – ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር)

By amele Demisew

November 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሪደር ልማቱ ታሪካዊቷን የሐረር ከተማ አዲስ ገጽታ እንድትላበስ እያደረገ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር)ና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በሐረር ከተማና በጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ውስጥ የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ፥ የኮሪደር ልማቱ በሐረር ከተማ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተመልክተናል።

በኮሪደር ልማቱ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችም ታሪካዊቷን የሐረር ከተማ ውብና ፅዱ በማድረግ አዲስ ገፅታ እንድትላበስ እያደረገ ነው ብለዋል።

በተለይም የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን የተሳለጠ እንዲሆን ከማስቻል ባለፈ ለዜጎቹ ምቹ እንዲሆን እያስቻለ መሆኑንም ነው ያነሱት።

በክልሉ ፍጥነትንና ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።