Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ጥላሁን ከበደ በሁሉም ዘርፎች እመርታ ማስመዝገብ እንደሚገባ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በሚሠራው ሥራ በሁሉም ዘርፎች እመርታ ማስመዝገብ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ አስገነዘቡ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በወቅታዊ የግብርና ልማት አተገባበር ላይ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡

አቶ ጥላሁን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በምናከናውናቸው ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ምርታማነታችንን ማሳደግ አለብን ብለዋል።

እመርታን በማስመዝገብ የቤተሰብ ብልጽግናን ማረጋገጥ መቻል አለብን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዋና ዋና ሰብሎችን ጨምሮ የቡና ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ብክነት ሳይኖር ጥራትን በማስጠበቅ ምርታማነትን ከፍ ማድረግ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማምረት የክልሉን ገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን መቀነስ እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡

የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራንም በትጋት ማከናወን እንደሚገባ ነው ያስረዱት፡፡

በአበበች ኬሻሞ

Exit mobile version