Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአይሻ 3 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም 83 ነጥብ 8 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአይሻ 3 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ አፈጻጸም 83 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የንፋስ ኃይል ማመንጫው 120 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ታስቦ እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን አሁን ላይ አፈጻጸሙ 83 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ መኮንን ገልጸዋል፡፡

ግንባታው ደረጃ በደረጃ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው÷ፕሮጀክቱ 80 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት እያስገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቀሪውን 40 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን የመትከል ሥራ ለማከናወንም የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መናገራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ አመልክቷል።

ተርባይኖችን የመትከል ሥራው በፋይናንስ አቅርቦት ምክንያት መዘግየቱን አስታውሰው÷ አሁን ላይ ተቋሙ አበዳሪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ አቅም ግንባታውን ለማጠናቀቅ ወስኖ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል።

Exit mobile version