የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጀመረ

By Feven Bishaw

November 12, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማከናወን ጀምሯል::

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት÷ በግምገማው የተያዘው እቅድ የተከወነበት መንገድ ይፈተሻል።

በዚህም የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና በድክመት የተለዩ ሥራዎችን ደግሞ በትኩረት መገምገም ተገቢ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

የሚታዩ ድክመቶች ሳይሸፋፈኑ መገምገማችን አንዱ የጥንካሬያችን ምንጭ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት፣ ጉቦኝነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት ለመፍታት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር እንዴት አቅዶ እንደሰራና ሃላፊነቱን እንደተወጣ መገምገም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።