አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያና የደንቢ ሎጅ ግንባታ የሥራ እንቅስቃሴ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የቤንች ሸኮ ዞን እንዲሁም የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኙ ሰራተኞችን በስፍራው ተገኝተው አበረታትተዋል።
አመራሮቹ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ የሥራ ሁኔታን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት እየተገነቡ ከሚገኙ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው በቤንች ሸኮ ዞን እየተገነባ የሚገኘው የደንቢ ሎጅ ግንባታ የሥራ እንቅስቃሴንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡