Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ለአውሮፓ ገበያ ተላኩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ተጓጉዘው ለአውሮፓ ገበያ መላካቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ቬጅ ፍሩ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የተባሉ የአትክልት ምርቶችን በመርከብ በማጓጓዝ ወደ ኔዘርላንድስ የመላክ ሥራ በዛሬው ዕለት ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

12 ቶን ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የአትክልት ምርቶችን ዘመናዊ የማቀዝቀዣና አዳዲስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ኮንቴነር በመጠቀም ምርቱ ጅቡቲ ወደብ ከደረሰ በኋላ በመርከብ እንደሚላክ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም መሰረት የአትክልት ምርቱ ከቆቃ ተነስቶ በመርከብ ተጓጉዞ በ23 ቀናት ውስጥ ኔዘርላድስ እንደሚደርስ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

Exit mobile version