Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ጥላሁን ከበደ በዲላ ዙሪያ ወረዳ የቡና ልማት የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ እየተከናወነ ያለውን የቡና ልማት የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው።

ጉብኝታቸው የተሻሻለ የቡና ልማት ተግባራትን እንዲሁም የቡና እሸት መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች የስራ እንቅስቃሴን ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል።

የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ብሩ÷ በክልሉ በነቅሎ ተከላና በአዲስ መሬት ላይ የቡና ልማትን ለማስፋፋት በተደረገ ጥረት የቡና ሽፋንን ከ228 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማድረስ ስለመቻሉ ተናግረዋል።

በዚህም በተያዘው የምርት ዘመን ከ34 ሺህ ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በቀጣይም በይርጋ ጨፌና በወናጎ ወረዳዎች መሰል የመስክ ምልከታ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version