አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት ለሆኑ ሴት ልጆች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ እንደሆነ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ዘመቻውን አስመልክቶ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ህፃናት እና አፍላ ወጣቶች መሪ ስራ አስፈፃሚ የክትባት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ አቶ መልካሙ አያሌው እንደገለጹት÷ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ክትባቱን ላላገኙ ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
የክትባት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሙያው አቶ ብርሃኑ በቀለ በበኩላቸው÷ ክትባቱን በዘመቻ መልክ ለሁሉም ለማዳረስ አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በየጤና ጣቢያ ከ9 ዓመት ጀምሮ ላሉ ሴት ልጆች በመደበኛ ፕሮግራም አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻልም መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡