የሀገር ውስጥ ዜና

በቢሾፍቱ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ለማስጀመር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

By Feven Bishaw

November 11, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የቢሾፍቱ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ለማስጀመር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት በማቅረብ ቢሾፍቱ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ጋር የተቀናጀ ሥራ ይሰራል ተብሏል።

ፍሬሕይወት ታምሩ ÷ስማርት-ሲቲ ከተሞችን ውብ፣ ማራኪ፣ ሳቢና ለሰው ልጆች ምቹ የማድረግ ሥራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት መተግበር ከተማዋን ከማዘመን ባለፈ ተጨማሪ ውበት እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡

በፈቲያ አብደላ