አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ በዘመነ ስልጣናቸው ቅድሚያ ሰጥተው ከሚተገብሯቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የሆነውን የስደተኞች እና የድንበር ጉዳዮችን እንዲያማክሯቸው ለቶም ሆማን ሹመት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ትራምፕ በኤክስ ገፃቸው እንዳስታወቁት÷ የቀደሞውን የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አፈፃፀም ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ቶም ሆማን የስደተኞችና የድንበር ጉዳዮች አማካሪ በመሆን አስተዳደራቸውን ተቀላቅለዋል።
በስደተኞች እና ድንበር ቁጥጥር ዙሪያ በቀድሞ የስልጣን ዘመናቸው ከሚያውቋቸው ቶም ሆማን የተሻለ ሰው የለም ብለዋል፡፡
ቶም ሆማን ስራቸውን ሲጀምሩ ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችን የማስወጣት ሂደትን በበላይነት እንደሚመሩት ትራምፕ አስገንዝበዋል።