የሀገር ውስጥ ዜና

ያለንን ጸጋ እያለማን ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን – አቶ አወል አርባ

By ዮሐንስ ደርበው

November 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ወደልማት በመቀየር ሀገራችንን ከፍ እናደርጋለን ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

አቶ አወል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ በተለይም በቱሪዝም መስኅብ ገና ያልተነኩ ትልልቅ የተፈጥሮ ሀብት የሆኑ ሥፍራዎችን በማልማት በቱሪዝም ዘርፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች አጠናክረን በመቀጠል የሀገራችንን ውበት ለዓለም እናሳያለን ብለዋል፡፡

የሚያኮሩ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ወደልማት በመቀየር ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን ሲሉም ገልጸዋል።