አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዎልቭስ፣ ብሬንት ፎርድና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋ፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረጉ 4 ጨዋታዎች ዎልቭስ ሳውዝ ሃፕተንን፣ ፉልሃም ክሪስታል ፓላስን በተመሳሳይ 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ብሬንትፎርድ ደግሞ ቦርንማውዝን 3 ለ 2 ረትቷል፡፡
ዌስትሃም እና ኤቨርተን ደግሞ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ የምሽት ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ምሽት 2፡30 ማንቼስተር ሲቲ ከብራይተን እንዲሁም 5 ሰዓት የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከአስቶንቪላ ጋር የሚደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡