አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታኗ ባሎቺስታን ግዛት በሚገኝ የባቡር ጣቢያ ላይ በተከሰት የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
በባቡር ጣቢያው ከ100 በላይ ተጓዦች እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን÷ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ60 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡
በፍንዳታው ከሞቱት ውሰጥ አብዛኞቹ ወታደሮችና የባቡር ጣቢያው ሰራተኞች እንደሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡