አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እና የሽግግር የጸጥታ ዝግጅቶች ክትትል እና ማረጋገጫ መካኒዝም (ሲትሳም) ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በመስጠት ለደቡብ ሱዳን ሰላም እና ፀጥታ መረጋጋት ኢትዮጵያ የቻለችውን ሁሉ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡