አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከጋቦን 200 ተማሪዎችን ተቀብሎ ሊያሰለጥን መሆኑን አስታወቀ።
ጋቦናውያን ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሏል፡፡
በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ የጋቦን ሪፐብሊክ አምባሳደር ሊሊ ስቴላ ንዶንግ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።