Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ቺሊ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከቺሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ግላሪያ ዴ ላ ፎንቴ ጋር ተወያይተዋል።

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ኢትዮጵያ የቺሊን የሴቶችን ተሳትፎ ያረጋገጠ የፓለቲካ ምህዳር ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የወጣቶችንና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ለማሳደግ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ እየተገበረች መሆኑን ገልጸዋል።

ከቺሊ ጋር በዘርፉ ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተመላከቱ ተግባራትን በመላ ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡

ግላሪያ ዴ ላፎንቴ በበኩላቸው ቺሊ ሴቶች ላይ ልዩ ትኩረት ያደረገ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዳላት ጠቅሰው÷ይህንን ተሞክሮ እስካአሁን እንደ ካናዳ ላሉ ሀገራት ማጋራቷን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በእነዚህና ሌሎች መስኮች ላይ የመግባቢያ ስምምነቶችን በመፈራረም ወደ ሥራ ለመግባት የቺሊ መንግስት ዝግጁ እንደሆነ መጥቀሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version