የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ-ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

November 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ-ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት የተለያዩ ውሣኔዎችን በማፅደቅ ተጠናቋል።

በውይይቱ በሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም በአፍሪካ ህብረት የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡

ይህ ስምምነት ለጥቃት ተጋላጭ ሴቶች እና ታዳጊዎች ፍትህ እንዲያገኙ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ሀገራትን ዝግጁነት ለማሳወቅ የተደረሰ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስምምምነቱ በተለያ የስራ ሃላፊዎች ውይይት ከተደረገበት በኋላ ለመሪዎች ስብሰባ ከመቅረቡ በፊት በአፍሪካ ህብረት አሰራር መሰረት የህግና ፖሊሲ ክፍል እንዲመለከተው ስምምነት ተደርጓል።

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ውይይ በተባበሩት መንግስታት የሴቶች ሁኔታ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የሚቀርበው የአፍሪካ የጋራ አቋምን በማፅደቅ መጠናቀቁን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡