Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል በጤና ኤክስቴንሽን ዘርፍ ውጤት ማምጣት መቻሉ ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በጤና ኤክስቴንሽን ዘርፍ ውጤት ማምጣት መቻሉ ተገለፀ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የክልሉ ጤና ቢሮ የ2016 ዓመታዊ የሴክተር ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንዳሉት÷ መሠረታዊ የሆነ የጤና አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ጤናማ ማህበረሰብን መገንባት ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

የጤና ተቋማት እጥረት ያለበት አካባቢ ተቋማትን በመገንባት ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ጥያቄ መመለስ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የጤና ባለሙያዎች በብቃት እና በተነሳሽነት ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ የማብቃት ስራ ይሰራል ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚህ ዓመት ለጤናው ኤክስቴንሽን ዘርፍ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል።

ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ÷ በ2016 በጀት ዓመት በጤናው ኤክስቴንሽን ዘርፍ ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ተደራሽነት እንዳይፋጠን የመድኃኒት መመዝበር እና የባለሙያዎች ተጠያቂነት ማጣት ተግዳሮት መሆኑን ገልጸው፤ በ2017 በጀት ዓመት ችግሩን ለመቅረፍ በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የጤና አግልግሎት አሰጣጥ የተሳለጠ እንዲሆን ከጤና ተቋማት በተጨማሪ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በነፃነት ሰለሞን እና ደብሪቱ በዛብህ

Exit mobile version