አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን እየጎበኙ ይገኛሉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ረፋድ ላይ ጎንደር ከተማ የገቡ ሲሆን÷ በቆይታቸው በከተማው የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህም የግንባታ ሂደቱ እየተፋጠነ የሚገኘውን የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን በመጎብኘት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።