አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን በዛሬው ዕለት ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ አድርጓል፡፡
ሌጎስ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን በደመቀ ሁኔታ አቀባበል እንዳደረገችም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ አመልክቷል፡፡
የናይጄሪያዋ ከተማ ሌጎስ በዚህ ልዩ እና እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላን በረራ የተጀመረባት የመጀመሪያዋ መዳረሻ ከተማ መሆኗም ተጠቁሟል፡፡