Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የመገናኛ ሬዲዮ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6ኛ ዕዝ የአንድ ኮር አባላት ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ለአሸባሪው ሸኔ ቡድን ሊተላለፍ የነበረ የመገናኛ ሬዲዮ መያዙ ተገልጿል፡፡

መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ አሊ ዲሮ ወደተባለ ቦታ ለአሸባሪው ቡድን ሊደርስ የነበረ 21 ዘመናዊ የመገናኛ ሬዲዮ ነው በሰሜን ሸዋ ዞን ፊቼ ከተማ የተያዘው፡፡

የመገናኛ ሬዲዮው የኮሩ አባላት ባደረጉት ብርቱ ክትትል መያዙን የኮሩ ዘመቻ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጌታሁን ደምሴ ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በወሊሶ ወረዳ ቀብሮት የነበረ 02 ክላሽ ከ280 ጥይት ጋር በተመሳሳይ ጥቆማ መያዙን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአሸባሪው ሸኔ ቡድንና ግብረ አበሮቹ በሕገወጥ መንገድ እያደረጉት ያለው ተግባር የሀገርን የልማት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመ መሆኑን ሃላፊውአስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version