Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በ”ከረሃብ ነፃ ዓለም” ጉባኤ ላይ ቀርቧል – ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በ”ከረሃብ ነፃ ዓለም” ጉባኤ ላይ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የ “ከረሃብ ነፃ ዓለም” ጉባኤን ስናጠናቅቅ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ተሳታፊዎች ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

40 ቢሊየን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በአረንጓዴዓሻራ መርሐ-ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው መቅረቡንም ገልጸዋል፡፡

በ’ኢትዮጵያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገትና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በዓለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና እንዳጠናከሩትም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡

አክለውም ፥ ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የዓለምአቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ ስለመሆኑም አንስተዋል።

 

Exit mobile version