Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 3 ነጥብ 75 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ተደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የ3 ነጥብ 75 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 5 ሺህ የሚሆኑ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች በሀገሪቱ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን÷ በዘላቂ ልማት በስነ-ምግባር እና በዲሞክራሲ ግንባታ ላይ በሰፊው እየሠሩ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

ዛሬ ይፋ የሆነው ገንዘብ ድጋፍ 75 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን የውስጥ አቅም ለማጎልበት፣ ንቁና ተጠያቂ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለመፍጠር፣ በማስረጃ የተደገፈ የፖሊሲ ውትወታ እንዲሁም በዲሞክራሲ ሂደቶች እና በግጭት አፈታት መንገዶች ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፕሮጀክቱ ከታቀፉት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ውስጥ ለመጀመሪያ 36 ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ዩሮ ድጋፍን አስመልክቶ የፊርማ ስነ -ስርዓት የተካሄደ ሲሆን÷ ድጋፍ የተደረገላቸው ሀገር በቀል ድርጅቶቹ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ እንደሚሠሩ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version