አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 28ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች የጋራ የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀምሯል፡፡
በንግድ፣ ፀጥታ እና የድንበር ጉዳዮች ላይ መወያየትን አላማው ያደረገው መድረኩ ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
መድረኩ የኢትዮጵያና የጅቡቲን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ብሎም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡
ውይይቱ የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክርና የቀጣይ አቅጣጫዎችም የሚቀመጡበት መሆኑ የተመላከተ ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በበረከት ተካልኝ እና ሰለሞን ይታየው